Home
Contested Knowledges in and through Asylum Litigation (ASYKNOW)

Amharic (አማርኛ)

“ስለ ጥገኝነት ይግባኞች ሂደቶች የተመለከቱ አከራካሪ እውቀቶች” (ASYKNOW) በሚል ርዕስ በሚካሄደው የምርምር ጥናት ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ ይፈልጋሉ? ASYKNOW በኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ስዊድን እና ጀርመን ውስጥ ለጥገኝነት ይግባኞች ሂደቶች ጥቅም ላይ የሚውሉትን የባለሙያ እውቀት እና ማስረጃ አጠቃቀም ያጠናል።

Main content

አላማ  

የጥገኝነት ጉዳዮች ለውሳኔ ሰጪዎች ለመወሰን አስቸጋሪ ሊሆኑ የሚችሉ ሲሆን ውሳኔው ጉዳዩ ለሚመለከተው ግለሰብ ከፍተኛ ውጤቶች አሉት። የባለሙያ እውቀት በጥገኝነት ይግባኞች ሂደቶች ላይ የሚወተውን ሚና የበለጠ ማወቅ አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን። የባለሙያ እውቀት እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እና ጥገኝነት ውድቅ ሲደረግ ይግባኝ በሚባልበት ወቅት እንዴት እንደሚፈተን በተሻለ ማወቅ አውሮፓ ውስጥ የጥገኝነት ሥርዓቱን ለማሻሻል ሊረዳ ይችላል። የባለሙያ እውቀት ለምሳሌ፡ የህክምና ሪፖርቶችን፣ የአገር መረጃን፣ እና የቋንቋ እና የእድሜ ፈተናዎችን ያጠቃልላል።

 

ምን እንደምናደርግ  

በጥገኝነት ይግባኝ ሂደቶች ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን (ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ጠበቆች፣ ዳኞች፣ ምስክሮች፣ አስተርጓሚዎች፣ ወዘተ) ማናገር እንፈልጋለን። በተጨማሪም በሂደቱ ላይ ያልዎትን ተሞክሮ የተመለከቱ ጥያቄዎችን እንጠይቅዎታለን። 

ጥናቱ በተጨማሪም በፍርድ ቤት ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ምልከታዎችን እንዲሁም የጉዳይ ሰነዶችና ውሳኔዎችን ማንበብን ያካትታል። 

መረጃው የትምህርት ርዕሰ አንቀጾችን እና መጽሀፎችን ለመጻፍ ያገለግላል። በተጨማሪም ለውሳኔ ሰጪዎች፣ ድርጅቶችና መገናኛ ብዙሀን ገለጻዎችን እናደርጋለን። ስሞችን እና የግል ባህሪያትን የምንቀይር በመሆኑ ምክንያት ከምንጽፈው ማንኛውም ነገር ውስጥ የእርስዎን ማንነት ለይቶ ማወቅ አይቻልም። 

ተሳትፎው በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው 

አንዳንድ መመለስ የማይፈልጓቸው ጥያቄዎች ካሉ ባይመልሱም ምንም አይደለም። በተጨማሪም ከፍርድ ቤት ጉዳይ የወሰድናቸውን ማስታወሻዎች እንድንጠቀም ባይፈልጉም ችግር የለውም። ፍላጎትዎን ብቻ ያሳቅቁን። በጥናቱ ላይ መሳተፍ ባይፈልጉ ወይም ቆይተው መረጃዎ እንዲሰረዝልዎ ለመጠየቅ ቢፈልጉ ይህ ምንም አሉታዊ ውጤቶችን አያስከትልብዎትም። 

ከተሳትፎው ጋር ተያያዥነት ያላቸው ማንኛውም ጥቅሞች ወይም ስጋቶች አሉ? 

በጥናቱ ላይ ከመሳተፍ ጋር በተያያዘ የሚገኙ ማንኛውም ቀጥተኛ ጥቅሞች ወይም የሚያጋጥሙ ስጋቶች አሉ ብለን አናምንም። በጥናቱ ላይ ለመሳተፍ ይምረጡም አይምረጡም ይህ በጥገኝነት ጉዳይዎ ላይ ተጽእኖ አይፈጥርም። ስለዚህ በተመለከተ ከቃለ መጠይቁ በፊት ተጨማሪ መረጃ እሰጥዎታለሁ። 

ማንኛውም የሚነግሩን ነገር በሚስጥር ይያዛል። ሆኖም ከባድ፣ በሌሎችም ሆነ በእርስዎ ህልውና ላይ አደጋ የሚያስከትል መረጃ የሚሰጡ ከሆነ ይህን ለሚመለከታቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በማሳወቅ የመርዳት ግዴታ አለብን። 

መረጃዎን እንዴት እንደምናስቀምጥ እና እንደምንጠቀም 

ይህ በበርገን ዩኒቨርሲቲ (niversity of Bergen) የሚመራ እና በአውሮፓ የምርምር/ጥናት ካውንስል የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ገለልተኛ ጥናት ነው። 

እርስዎን የተመለከተ መረጃዎን የምንጠቀመው እዚህ ላይ ለገለጽናቸው ዓላማዎች ብቻ ነው። ከጥናቱ ለመውጣት ከፈለጉ በዚህ ሰነድ ላይ የቀረበውን የግንኙነት መረጃችንን በመጠቀም እኛን ማናገር ይችላሉ። 

ሁሉም ዳታ ደህንነቱ ወደተጠበቀ የመረጃ ቋት የሚዘወርና የሚቀመጥ ከመሆኑም በተጨማሪ ስምዎን ጀምሮ የግንኙነት መረጃዎን ለይተን እንይዛለን። መረጃዎን ከምርምር ጥናት ቡድኑ ውጭ ለማንኛውም ሰው ማጋራት አይፈቀድልንም። 

ፕሮጀክቱ ካበቃ በኋላ መረጃው ማንነትን እንዳይገልጽ ይደረጋል። ይህ የሚሆነው ቢበዛ እስከ 2030 መጨረሻ ድረስ ነው። 

ተጨማሪ መረጃ ከየት ማግኘት እችላለሁ? 

ጥናቱን በተመለከተ ማንኛውም ጥያቄዎች ካሉዎት ወይም መብቶችዎን ለመጠቀም ከፈለጉ እባክዎ የሚከተሉትን ያነጋግሩ፡ 

ዋና መርማሪ: Dr. Marry-Anne Karlsen፣ የበርገን ዩኒቨርሲቲ፣ የማህበራዊ አንትሮፖሎጂ መምሪያ፣ ኢሜይል፡ marry-anne.karlsen@uib.no፣ ስልክ፥ +47 55 58 89 31  

የዳታ ጥበቃ ኦፊሰር፥ Jannecke Helene Veim፣ የበርገን ዩኒቨርሲቲ፣ የተነጻጻሪ ፖለቲካ መምሪያ፣ የመ.ሣ. ቁጥር 7800፣ NO-5020 በርገን ኖርዌይ፣ ስልክ፥ +47 930 30721 / +47 555 82029፣ ኢሜይል፥ Janecke.Veim@uib.no